Fana: At a Speed of Life!

በደሴ የብልፅግና ፓርቲ በጉባኤው ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ የብልፅግና ፓርቲ በፓርቲው የጉባኤ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የስራ ዕድልና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ መድረኩ የፓርቲውን ውሳኔዎች ለህዝቡ በቀጥታ የምናደርስበት ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው ÷ ከተማዋ ከወረራ በኋላ ያለችበትን ሁኔታ የገለፁ ሲሆን÷ የከተማው ነዋሪዎች የዳግም ወረራ ስጋት እንዳለበትና ራሱን ለመከላከል መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግለት እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል።

ህገወጥ ጦር መሳሪያ አያያዝ፣ የኑሮ ውድነት እና የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ከተማዋ ከወረራ በኋላ እያስተናገደች ያለው ችግር መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በእሌኒ ተሰማ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.