Fana: At a Speed of Life!

የኑሮ ውድነት ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑሮ ውድነት ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የወከሉት የምክር ቤት አባላት ከመረጧቸው ህዝብ ጋር በተወያዩበት ወቅት የኑሮ ውድነት ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በሀገሪቱና በከተማው ስላለው የፀጥታና የመልካም አስተዳደር ችግር፣ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ተጀምረው ስላልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፣ የሸማች ማህበራት ተገቢ ያልሆነ እና የታችኛው ማህበረሰብን ያላማከለ አቅርቦትን በተመለከተ መንግስት ሊያስተካክላቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ህዝቡን እያማረረ ስላለው የኑሮ ውድነት መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ነው የከተማዋ ነዋሪዎች ያነሱት።

ተመራጮቹ በበኩላቸው÷ ህዝቡ ከወረዳ ጀምሮ እያነሳቸው ያሉት ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቷቸው መልስ እንዲያገኙ ከወረዳ፣ ከክፍለ ከተማና ከከተማ አመራሮች እንዲሁም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ ነው የገለጹት፡፡

በህዝብና እና በመንግስት መካከል ድልድይ በመሆን የተጣለባቸውን አደራ እንደሚወጡ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.