Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት ኢንክ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል።ኩባንያው በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ 3 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተሰሩ የፍለጋ እና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የማሳወቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ያካሂዳል ተብሏል።

በስምምነት ስነስርአቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን የኩባንያው ተወካዮች እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በጥበበስላሴ ጀንበሩ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.