ዓለምአቀፋዊ ዜና

የኮሮና ቫይረስ ከጣሊያን ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት እየተስፋፋ ነው

By Meseret Demissu

February 26, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ከጣሊያን ወደ ሎሌች የአውሮፓ ሀገራት እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ በሀገራቸው መከሰቱን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ መሰረት ቫይረሱ በኦስትሪያ፣ ክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን መከሰቱ ተገልጿል።

ቫይረሱ ወደ ሀገራቱ የተሰራጨው ከጣሊያን በመጡ ሰዎች አማካኝነት መሆኑ ነው የተነገረው።

በተመሳሳይም ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አልጀሪያም የኮሮና ቫይረስ ከጣልያን በመጣ ግለሰብ አማካኝነት መግባቱን አረጋግጣለች።

በላቲን አሜሪካዋ ሀገር ብራዚልም ከጣሊያን በተመለሰ ግለሰብ ኮሮና ቫይረስ መከሰቱ ታውቋል።

በጣሊያን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 300 የደረሰ ሲሆን፥ 11 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision