Fana: At a Speed of Life!

በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አንደኛ ሆና በማጠናቀቋ እንኳን ደስ አለን- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም አንደኛ ሆና በማጠናቀቋ ለአትሌቲክስ ቡድኑ አመራርና አባላት በሙሉ የእንኳ ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ደመቀ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷በውድድሩ የነበራችሁን እጅግ አስደሳች ተሳትፎ እና ውጤት ተከትሎ የሀገራችን ሰንደቅ አላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ስላደረጋችሁ ኮርተንባችኋል ብለዋል፡፡
በዚህም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን ነው ያሉት።
የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከዓለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወቃል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ጾታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡
ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.