Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ውሳኔዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ህዝባዊ የውይይት መድረክ በቦንጋ እና በሚዛን አማን  ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

 

እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ  የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ  ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች  የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

 

መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ እንደሚመክር ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በሚዛን አማን  ከተማ  እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ፓርቲው በቅርቡ ባካሄደው ታሪካዊ ጉባዔ በወሰናቸው ውሳኔዎችና ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ለውሳኔዎቹ ተፈጻሚነት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ውይይቱን የመሩት የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ  ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዲሁም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ማስረሻ በላቸው እና የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪው አቶ ቀበሌ መንገሻ ጥሪ አቅርበዋል።

 

የዞኑና የከተማው ህዝብ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ፣ ለኑሮ ውድነት መሻሻል፣ ለህዝባዊ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል፣ ለኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ለአከባቢው ሁለንተናዊ ብልጽግና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግሥት አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት እንደሚሰራ የውይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.