Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የከፍተኛ የሮኬት ሞተር ሙከራን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቋን ገለፀች

አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና ሎንግ ማርች 5 ለተባለው ሮኬት የተነደፈውን የሮኬት ሞተር ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቋን ገልፃለች፡፡
 
የቻይና ኤሮስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው በትናንትናው እለት የተደረገው የሮኬት ሞተር ሙከራ ተጠናቆ አሁን ላይ ወደ ሮኬቱ የመጨረሻ መገጣጠሚያ ክፍል ለመግባት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
 
ኮርፖሬሽኑ በተጨማሪም የሮኬት ሞተር ሙከራን የተሳካ ለማድረግ ከ20 በላይ ተጨማሪ ሙከራዎች እንደሚደረጉም አመላክቷል፡፡
 
ቻይና በዚህ አመት ዌንቲያን እና መንግቲያን የተባሉ የጠፈር ጣቢያዎች ግንባታ የምትጨርስ ሲሆን 150 ካሬ ሜትር ቦታ ያለው የጠፈር ጣቢያ ግንባታው ስድስት የጠፈር ተመራማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን የዘገበው ሲ ጅ ቲ ኤን ነው፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.