ናይጄሪያ በአፍሪካ ትልቁን የማዳበሪያ ፋብሪካ ስራ አስጀመረች
አዲስ አበባ፣መጋቢት 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያ በ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ያስገናበችውን በአፍሪካ ትልቁን የማዳበሪያ ፋብሪካ በይፋ ስራ አስጀመረች።
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ በመክፈቻ ስነ ስርቱ ላይ እንደተናገሩት በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የዋጋ ንረት የዓለም ማህበረሰብ ተፅዕኖ ውስጥ እንዳይወድቅ ናይጀሪያ በሰብል ማዳበሪያ አቅርቦት ረገድ የራሷን ሚና ትወጣለች ብለዋል፡፡
የንግድ ከተማ በሆነቸው ሌጎስ የተገነባው የዳንጎቴ ማዳበሪያ ፋብሪካ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር አገሪቱ ወደ ውጭ በምትልከው የማዳበሪያ ምርት ከፍተኛ ገቢ ታገኛለች ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ፋብሪካው በዓመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የሰብል ማዳበሪያ የማምረት አቅም እንዳለውም ነው የተናገሩት።
የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ጎድዊን ኢምፊሌ በበኩላቸው የፋብሪካው መከፈት የናይጀሪያን የማደበሪያ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታ እምነታቸውን ገልጸዋል።
ግብርና ለናይጄሪያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሲሆን ሀገሪቱ በ2021 ከ173 ቢሊየን ዶላር ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ 25 ነጥብ 8 በመቶውን የግብርና ምርት ይሸፍናል።
ሆኖም የናይጀሪያ ገበሬዎች አልፎ አልፎ ማዳበሪያ እና የተሻሻሉ ችግኞች አቅርቦት ችግር ያጋጥማቸው እንደነበር አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!