Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የቤት ውስጥ የ4ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የቤት ውስጥ የአራተኛ ትውልድ (4ጂ) የኢንተርኔት አገልግሎት ጀመረ።
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ 4ጂ /home 4g wttx/ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ለመኖርያ ቤት አገልግሎት ማቅረቡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል፡፡
ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ቦታዎች በአማራጭነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አራተኛ ትውልድ (4ጂ) ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ነው ተብሏል፡፡
አገልግሎቱ ደንበኛው በመኖሪያ አካባቢያቸው ወይም በመረጡት ቦታ ተወስኖ የሞባይል ኔትወርክን በመጠቀም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ ማግኘት የሚያስችል አማራጭ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟለት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡
በቅድስት ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.