የሀገር ውስጥ ዜና

104 ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Tibebu Kebede

February 26, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 104 ኢትዮጵውያን በዛሬው ዕለት ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ ኢሪንጋ በሚባለው ግዛት በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ የቆዩ መሆናቸውን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።