ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች የሥራ መመሪያ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለ27 አምባሳደሮች የሥራ መመሪያ እና የሹመት ደብዳቤ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ አገራት ለተሾሙ አምባሳደሮች በብሔራዊ ቤተ መንግስት የሽኝት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የሥራ መመሪያ እና የሹመት ደብዳቤ የተሰጣቸው÷ በቆንስላ ጀኔራልነት እና በምክትል ሚሲዮን መሪነት በውጭ ሀገራት እና በሀገር ውስጥ ለሚሰሩ 27 አምባሳደሮች ነው፡፡
ዲፕሎማሲ የሀገርን ቀጣይነት ከሚያረጋግጡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጸው÷ አምባሳደር ሆኖ በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን መወከልም ይህንኑ ኃላፊነት መሸከም እንደሆነ ነው ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ያስገነዘቡት፡፡
አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያን በሚወክሉባቸው ሀገራት÷ የሀገር ገጽታ መገንባት ላይ እና ኢትዮጵያ ተደማጭ እንድትሆን በማድረግ ረገድ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸውም ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው÷ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴው የብሔራዊ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ፤ በሀገራት መካከል ጥሩ ወዳጅነት መፍጠር በሚቻልበት መንገድ እና ተደማጭነትን ማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
በሜሮን ሙሉጌታ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!