Fana: At a Speed of Life!

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለ3 ወራት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት
የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘም ተደርጎ አንደነበርም አይዘነጋም፡፡

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህልን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነው እንዲሻገሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.