Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት እርዳታ ለጋሹ ማህበረሰብ ለትግራይ ክልልና በጦርነቱ ለተጎዱ ሌሎች ክልሎች የሚያቀርበውን እርዳታ እንዲያሳድግ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 16፣2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት እርዳታ ለጋሹ ማህበረሰብ ለትግራይ ክልል እና በጦርነቱ ለተጎዱ አማራና አፋር ክልሎች የሚያቀርበውን እርዳታ እንዲያሳድግ ጥሪ አቀረበ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መኸመት የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን በማድነቅ መግለጫ አውጥተዋል።

በዚሁ መግለጫቸው ላይ እንደጠቆሙትም የመንግስት ውሳኔ በክልሉ እርዳታን ለሚሹ ዜጎች ለመድረስ አስፈላጊ በመሆኑ ኮሚሽኑ በአወንታ ይወስደዋል።

ሁሉን አቀፍና በድርድር በሚመጣ የተኩስ አቁም ላይ ሁሉም ወገን እንዲደርስ ህብረቱ ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም የህብረቱ የአፍርካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ከሁሉም ወገን እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ግጭቱን በፍጥነት ለመቋጨት የጀመሩትን ጥረት እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.