Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ ፌዴሬሽን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ኢትዮጵያና ሩስያን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከሩሲያ ፌዴሬሽን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ከሆኑት ፒተር አሞሶቭ ጋር ተወያዩ።

በሩሲያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩስያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ፒተር አሞሶቭ ጋር ባካሄዱት ውይይት፥ ስለኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከማስረዳታቸውም በተጨማሪ በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ቱሪዝም ዘርፍ ያሉንን እምቅ ሃብቶች አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተለይም የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር እንዲረዳ የምክር ቤት አባላትንም ሆነ ሌሎች ፍላጎት ያላቸውን አካላት በማስተባበር አገራችንን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡

ፒተር አሞሶቭ በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ማብራሪያና የጉብኝት ግብዣ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ የሁለቱን አገራት የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውም ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.