የሀገር ውስጥ ዜና

በቱሪዝም ልማት ዘርፍ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

By Meseret Awoke

March 26, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቱሪዝም ልማት ዘርፍ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ አግባቦች ላይ ምክክር ተደረገ፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፥ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክልሉ ጋር አብሮ ለመስራት መፈለጉን አመስግነው ፥ የሲዳማ ክልልም በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው ፥ ያሉንን የቱሪዝም ሃብቶች በማወቅና በማልማት ላይ እንዲሁም በማስተዋወቅና ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ላይ በሀገር ደረጃ ክፍተት በመኖሩ ይህንን ለመፍታት የምክክር መድረኩ አስፈልጓል ብለዋል።

በዘርፉ የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!