Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከኳታር ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር በዶሃ ተወያዩ።

ውይይታቸውን ያደረጉት ከዶሃ ፎረም ጎን ለጎን ተገናኝተው።

በውይይታቸው ላይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ሃሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፥ በቀጣይ የሁለቱን ሃገራት ትብብር እና ወዳጅነት በሚያጠናክሩ ነጥቦች ዙሪያም መክረዋል።

በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ከኳታር ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ካሊፋ ጃሲም አል ኩዋሪ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የኳታር ልማት ፈንድ በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ አቶ ደመቀ ያደነቁ ሲሆን፥ የሁለቱን ሃገራት ህዝብ ለህዝብ አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልፀዋል።

የኳታር ልማት ፈንድ በኢትዮጵያ ከማህበረ ኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ በሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉ የሁለቱን ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው እምነታቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.