የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአፋር ክልል ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና በጦርነቱ የወደሙ ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማቋቋም የሚውል ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
በዚህም በጥሬ ገንዘብ 400 ሺህ ብር ፣ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የፅዳት እቃዎች ፤ ከ787 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የታሸጉ ምግቦች ፣ ከ1 ሚሊየን 830 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮች ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ፣ ሼልፍ ፣ ወንበሮች እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ላይ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል አለዲን አለሳ÷ የአዲስ አበባ ፖሊስን ጨምሮ መላው የፀጥታ አካላት ከዋና ተልዕኳቸው ባሻገር በመሰል ሀገራዊ ጥሪ ወቀት ካላቸው ላይ ቆርሰው ለወገኖቻቸው ድጋፍ ማድረጋቸው ሕዝባዊነታቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላትም ላደረጉት ድጋፍ በአፋር ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት ረዳት ኮሚሽነር መንገሻ ሞላ በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፍክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ÷ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው ፤ በጀግንነት እንጠብቃለን ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በድጋፋችን እናረጋግጣለን” በሚል መርህ ድጋፉ መደረጉን አስታውቀው ወደፊትም ድጋፉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!