Fana: At a Speed of Life!

በልደታ ክ/ከተማ ከ162 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ከ162 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና ግንባታቸው የተጠናቀቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀዋል።

ከንቲባዋ በልደታ ክፍለ ከተማ የጤና፣ የትምህርት፣ የስፖርት ማዘውተሪያን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 82 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነው መርቀው የከፈቱት።

በክፍለ ከተማው የተመረቁት 82 ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ተጠቃሚ ለማድረግ የተገነቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ግንባታቸው ተጠናቆ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የተማሪ ምገባ አዳራሾች፣ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትና ሌሎችም ይገኙበታል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር፥ ለፕሮጀክቱ ከ162 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ገልጸው፥የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ብለዋል።

በጀማል አህመድ

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.