በህልውና ዘመቻው በጀግንነት ለተሰዉ እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የሚሊሻ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው የእውቅና መርሀ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህልውና ዘመቻው በጀግንነት ለተሰዉ እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ የሚሊሻ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው ከ27 ሚሊየን 600 ሺህ ብር በላይ የማበረታቻ ገንዘብ ሰጦታና የእውቅና መርሀ ግብር በሸዋሮቢት ከተማ ተካሄደ።
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ባምላኩ አባይ÷ የሽብር ቡድኑ ህወሃት የተለያዩ አካባቢዎችን ሲወር በሰላሙ ገዜ የልማት አርበኛ የሆነው የሚሊሻ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ከፍተኛ መስዕዋትነት በመክፈል አሸባሪውን ቡድን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል ነው ያሉት።
ለሀገርና ለወገናቸው ሲሉ መስዋትነት ለከፈሉ ለእዚህ የሚሊሻዎች እውቅና ለመስጠት በሸዋሮቢት ከተማ ከ12 ወረዳዎች ለተውጣጡ ከ220 በላይ የሚሊሻ ቤተሰቦችና አባላት ከ27 ሚሊየን 600 ሺህ ብር በላይ ተበርክቷል ብለዋል፡፡
የተሰጠው እውቅና ለከፈሉት የህይወት መሰዋትነትና ጀግንነት የሚተካ ሳይሆን መንግስት ውለታቸውን መቼም እደማይረሳ ለመግለፅ ነው ብለዋል።
ይህ የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ለነባሩና አሁን በአዲስ እየተቀላቀለ ላለው የሚሊሻ ኃይል በቀጣይ ለሀገራቸው ሰላምና ደህንነት የበለጠ እዲሰሩ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልጸዋል።
እውቅናውን ያገኙት በጀግንነት የተሰዉ የሚሊሻ ቤተሰቦችና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሚሊሻዎችም መንግስት ለሀገርና ለወገን ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን በዚህ መልኩ ማገዙ የሚያሰመሰግነው እንደሆነ ተናግረዋል ።
በአበበ የሸዋልዑል
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!