Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጃንጥራር አባይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የከተማ ግብርናን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ56 ሄክታር መሬት ላይ የከተማ ግብርናን አስጀመሩ።
በከተማዋ መሬት ጦም እንዳያድርና የፍጆታ ምርትን ለከተማው ህዝብ ለማቅረብ “ምግባችን ከደጃችን” በሚል መሪ ሃሳብ በመላው አዲስ አበባ ስራው መጀመሩ ይታወሳል።
የዚሁ አካል የሆነ ዝግጅት በምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አማካኝነት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የከተማ ግብርና ስራ ተጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ ወደ ከተማ ግብርናው ለተቀላቀሉ አዳዲስ የስራ እድል ተጠቃሚዎችም የመስሪያ ቦታ እና ሼድ ርክክብ መደረጉን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.