Fana: At a Speed of Life!

ማህበረሰቡ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናውን እየጠበቀ የእግርና ሳይክል ጉዞን እንዲያጎለብት ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ማህበረሰቡ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናውን እየጠበቀ የእግርና የሳይክል ጉዞን እንዲያጎለብት ጠይቀዋል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር ሳምንታዊ ከተሽከርካሪ ነፃ የብስክሌተኞች እና የእግረኞች ቀን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በዚሁ ወቅት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደገለጹት÷ እንደ ሀገር እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል አማራጭ ስትራቴጂ ተወስዶ እየተተገበረ ያለውን የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረፅ እየተሠራ ነው፡፡
በመላው ሀገሪቱ ወርሃዊ የንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን የህብረተሰቡን በእግር እና በሳይክል የመጠቀም ባህል ለማጎልበት ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው÷ በዚህም አዎንታዊ ለውጥ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ድሬ ዳዋ ከተማም ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው የአስተዳደሩ ክልል ሳምንታዊ የሞተር አልባ የእግረኞች እና ብስክሌተኞች ቀንን አውጃለች ብለዋል፡፡
የህብረተሰባችን ጤና ያሳስበናል ያሉት ከንቲባው፥ ለዚህም የእግር እና የሳይክል ጉዞ ባህል እንዲጎለብት እና የትራፊክ አደጋ እንዲገታ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ያለን ትብብርና ትስስር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ በየሳምንቱ እሁድ ከጥዋት 12 ሰዓት እስከ 6 ሰአት የከተማዋ ጎዳናዎች ከድንገተኛ አገልግሎት እና ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች ውጭ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ነጻ በመሆን ለእግረኞች እና ብስክሌተኞች ብቻ ክፍት ይሆናል መባሉን ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.