Fana: At a Speed of Life!

በአትሌቲክስ ሻምፒዮና መከላከያና ኢትዮ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለቦች የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አገኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መከላከያና ኢትዮ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለቦች የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡

 

ዛሬ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ስታዲየም በተካሄደው ውድድር÷ በሴቶች አሎሎ ውርወራ የመከላከያዋ አትሌት ዙርጋ ኡስማን 13 ነጥብ 56 ሜትር በመወርወር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

 

አትሌት መርሃዊት ጸጋዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12 ነጥብ 24 ሜትር እንዲሁም ሌላኛዋ የመከላከያ አትሌት አመለ ይበልጣል 12 ነጥብ 16 ሜትር በመወርወር የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

 

በወንዶች ስሉዝ ዝላይ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለብ ተወዳዳሪ ክችማን ኡጁሉ 16 ነጥብ 3 ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳሊያ ለክለቡ አስገኝቷል።

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ዶል ማች 15 ነጥብ 79 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አትሌት በቀለ ጅሎ 15 ነጥብ 54 ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ወጥቷል።

 

በአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት የ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.