“ኤች አር 6600” እና ‘’ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” የተሰኙ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።
የተቃውሞ ሰልፉ በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ “ካፒቶል ሂል” ፊት ለፊት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በዚህም አሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተጨማሪ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን በሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር ከዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተቃውሞ ሰልፉ “ኤችአር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎች የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጎዳ እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚያበላሹ በመሆናቸው ሊሰረዙ ይገባል የሚሉ መልዕክቶች በተሳታፊዎች እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡
“ማዕቀብ መጣል ለኢትዮጵያ ጉዳትን እንጂ ምንም ጥቅም አያስገኝም ፤ ጎጂ የሆኑት ረቂቅ ሕጎች ውድቅ መደረግ አለባቸው” የሚሉ መፈክሮችም እየተላለፉ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!