Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦች በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
የፍርድ ቤቱ ዳኛ ኤልሳቤት ታደሰ÷ ኦብሳ አደም እና ጋዲሳ አልዩ የተባሉ ህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች 4 ታዳጊ ሴቶችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመውሰድ ከምዕራብ ሐረርገጌ ዞን ሚጨታ ከተማ ወደ ድሬዳዋ በማጓጓዝ ላይ እያሉ መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጭሮ ከተማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
ታዳጊዎቹ የ16 እና 17 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው ጠቁመው፥ በድርጊቱ ተከሰው የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ግለሰቦች “የሳዑዲ አረቢያ መንገድ ሰላም ነው ትምህርታችሁን ብዙ ገንዘብ አግኝታችሁ ከመጣችሁ በኋላ ትቀጥላላችሁ” እያሉ እንዳታለሏቸው በሰጡት የእምነት ቃል ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ዳኛዋ አክለውም ታዳጊዎችን ከትምህርታቸው እያስተጓጎሉ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ድንበር አሻግረው ለሌሎች ደላሎች እንደሚያስረክቡ በምርመራ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው ፍርድ ቤት የፖሊስና ዐቃቤ ሕግ የምርመራ ውጤትን አመሳክሮ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.