Fana: At a Speed of Life!

መዳረሻቸው ቃሊቲ ወደብና ተርሚናል የሆኑ የመልቲ ሞዳል ኮንቴነሮችን በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መዳረሻቸው ቃሊቲ ወደብና ተርሚናል የሆኑ የመልቲ ሞዳል ኮንቴነሮችን በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ነው ከሞጆ ወደብና ተርሚናል በተጨማሪ የእንዶዴ ባቡር ጣቢያን በመጠቀም መዳረሻቸው ቃሊቲ ወደብና ተርሚናል የሆኑ የመልቲ ሞዳል ኮንቴነሮችን በባቡር ማጓጓዝ የጀመረው፡፡

ባቡሩ አገልግሎት በጀመረበት ባለፈው ሳምንት በአንድ ጊዜ 104 ቲ ኢ ዩ (ባለ ሃያ ጫማ) ኮንቴነሮች ይዞ የመጣ ሲሆን÷ ኮንቴነሮቹ እንዶዴ ባቡር ጣቢያ እንደደረሱ በፍጥነት በተሽከርካሪዎች እየተጫኑ በቅርብ ርቀት ወደሚገኘው ቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ተጓጉዘዋል መባሉን ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እነዚህ 104 ኮንቴነሮች በተሽከርካሪዎች ቢጓጓዙ ከጂቡቲ ቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ለመድረስ ከ3 እስከ 4 ቀናትን ይወስዱና 52 ተሽከርካሪዎችን ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን ÷ በባቡር በመምጣታቸው ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ በሰዓታት ውስጥ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የድርጅቱን አገልግሎት አሰጣጥ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ ለማድረግ ማስቻሉ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.