ከ655 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከ655 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተመደበለትና በ137 ሄክትር መሬት ላይ የሚገነባው የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ስራ ተጀመረ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወጪ 274 ሚሊየን ብር የካሳ ክፍያው የተሸፈነ ሲሆን÷ ለግንባታው የሚያስፈልገው ከ655 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ደግሞ በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
የግንባታው ተቋራጭ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽ ስራዎች ኮርፖሬሽን የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በ2ዓመት ከ8 ወር ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ውል ይዞ እየሰራ መሆኑን ከደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!