Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በመመለሱ ሂደት የመጀመሪያዎቹ ዛሬ ወደ ሀገራቸው ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሂደት ተጀምሯል፡፡
ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎችን ለመመለስ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡
የዚሁ ዕቅድ አካል የሆነው የመጀመሪያው ዙር ተመላሾች ዛሬ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡
ተመላሾቹን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዛሬ ማለዳ በመጀመሪያው በረራ ከሪያድ 157 ህጻናትንና 341 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች ገብተዋል።
ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ላሉት ዜጎች በጊዜያዊነት የሚያርፉበት ቦታም ተዘጋጅቷል።
በሳዑዲ አረቢያ ከ750 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩ ሲሆን፥ ከ450 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በህገወጥ መንገድ እንደሚኖሩ ይታመናል።
ከእነዚህ ውስጥም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ከ102 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መንግስት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።
በታሪኩለገሰ እና መሀመድ አሊ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.