Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና ሐረሪ ክልል አርሶ አደሮች ተጠቃሚነትን ሊያጠናክሩ በሚችሉ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ከተመራው ልዑክ ጋር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የኦሮሚያ እና የሐረሪ ክልል አርሶ አደሮች ተጠቃሚነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ተግባራዊ ለማድረግ የታሰቡ ፕሮጀክቶች ግድብ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ሲሆ÷ ፕሮጀክቶቹም በኦሮሚያና ሐረሪ ክልሎች አዋሳኝ በሆነው ኤረር ወረዳ አካባቢ እንደሚከናወኑ ነው የተገለጸው።
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ውይይት ተካሂዷል።
በተለይም በእስራኤል መንግስት የሚደገፈው ፌር ፕላኔት በተሰኘው ፕሮግራም አማካኝነት ለአርሶ አደሩ የተሻሻሉ ዝርያዎች እንደሚቀርቡ መገለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.