Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና ጤና ተቋማት ከ10 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓባይ ባንክ ሠራተኞች እና ፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ለሰሜን ወሎና ለዋግ ኽምራ ማህበረሰብ እንዲሁም ጤና ተቋማት ድጋፍ አደረጉ፡፡
የዓባይ ባንክ ሠራተኞች በሰሜን ወሎ እና ዋግ ኽምራ በድርቅና ረሀብ ለተጎዱ ወገኖች 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 1 ሺህ ኩንታል ዱቄት ለአማራ መልሶ ማቋቋምና ልማት ድርጅት ማስረከባቸውን ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ ፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ጤና ተቋማት 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸውን የሕክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል የክላስተር አስተባባሪ አቶ መብራት ከበደ÷ ድጋፉ ለአምደወርቅ እና ፅፅቃ ሆስፒታሎች እንዲሁም በ24 ጤና ጣቢያዎች የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት የሚያግዝ መሆኑን አመልክተዋል።
በድጋፉ የላቦራቶሪ፣ የማዋለጃ፣ የመተንፈሻ መርጃና የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያዎች፣ ዊልቸር፣ የህፃናትና የአዋቂዎች አልጋ እንዲሁም ከአንገት በላይ መመርመሪያ መሳሪያዎች መካተታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ÷ ድጋፉ በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋምና የነበራቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ለማሻሻል እንደሚያስችል ገልጸው ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም የጤና ተቋማትን የግብዓት እጥረት በመለየት መሰል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.