Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዘንድሮው የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የተሳተፉ ዜጎችን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስትዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዘንድሮው የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የተሳተፉ ዜጎችን አመሰገኑ።

አቶ ሽመልስ በምስጋና መግለጫቸው፥ የክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መስተጋብሩን በማጠናከር ብልጽግና ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

“ህዝባችን በአዳዲስ የልማት ሃሳቦች የተደገፉ የልማት ዕቅዶች ሲቀርቡለት ተዓምር መስራት እንደሚችል አሳይቷል” ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፥ “በመደመር መንገድ የሁሉንም ብልፅግና እናረጋግጣለን የምንለውም በህዝባችን ትልቅ ተሥፋ ስላለን ነው” ብለዋል።

“የበጋ ስንዴ ምርትም ከባዕዳን እጅ ሊያድነን እንደሚችል ህዝባችን በሠራቸው የልማት ሥራዎች አረጋግጧል” ነው ያሉት።

በዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ህዝቡ በመንግስት በጀት መሸፈን የማይችሉ የበርካታ ቢሊየን ብር የሚገመት ስራንም ሰርቶ ማሳየቱን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገዳ ሥርዓት በህዝቡ ውስጥ የኖረ እና የሚተገበር በመሆኑ ህጋዊ መሠረት ለማስያዝ እየተሰራ እንደሚገኝ ነው የጠቆሙት።

በመረዳዳት ባሕል በሚሊየኖች የሚቆጠር ህዝብ መጥፎውን ጊዜ እያሳለፈ አንደሚገኝ በመግለፅ፥ ህዝቡ የተጠሙትን በማጠጣት፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተራቡትን በመመገብ ደግነትን በማሳየቱም አመስግነዋል፡፡

በዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ዕቅድ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ በመስራት 2 ነጥብ 41 ሚሊየን ሄክታር መሸፈን መቻሉንና ጉልበቱም በገንዘብ ሲተመን ከ9 ነጥብ7 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚሆን ነው ይፋ ያደረጉት።

ይህም በህብረ ብሔራዊ አንድነት የልማት ድል ማስመዝገብ የጀመረው ህዝብ ወደ ብልፅግና ለሚያደርገው ጉዞ ስኬት ማሳያ መሆኑን ነው ያስረዱት።

የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ውጤታማ ለማድረግ የችግኝ መትከያ ቦታ በማዘጋጀት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ርዕሰ መስተዳድሩ አመስግነዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.