የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተመድ የካፒታል ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

March 31, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተባበሩት መንግስታት የካፒታል ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ፕሪቲ ሲንሃ እና ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ሂሳ ኢሳ ቡሁመይድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ዱባይ በተዘጋጀውን የዓለም መንግስታት እና የሴቶች ተሳትፎ በመንግስት አመራርነት ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።

ከንቲባዋ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካፒታል ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ፕሪቲ ሲንሃ እና ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ሂሳ ኢሳ ቡሁመይድ ጋር መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር እና በሌሎች ጉዳዮች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው መንገዶቸ ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባዋ በዱባይ ኤክስፖ ማዕከል የኢትዮጵያ እንዲሁም የሌሎች ሃገራት ፓቪሊዮን መጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!