Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ቢሮዎች በዘርፉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለመግባባት የሚያስችል የጋራ መድረክ ማካሄድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል የጤና ቢሮዎች እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በዘርፉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለመግባባት የሚያስችል የጋራ መድረክ ማካሄድ ጀመሩ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ÷ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም፣ ተግዳሮቶች እና የተገኙ ልምዶችን በጋራ ለመገምገምና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ለመግባባት ይረዳል ብለዋል፡፡

የተለያየ ግጭት ያለባቸውን ሁሉንም አካባቢዎች በአግባቡ በመዳሰስ እና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ፣ በሆስፒታሎች እና በጤና ተቋማት አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት የተቋረጡ የህክምና አገልግሎቶች መልሰው እንዲጀምሩ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት ዶክተር ደረጄ÷ ይህም በመድረኩ በትኩረት የሚገመገም አጀንዳ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሴክተሩ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም፣ የጤና ዘርፍ የፋይናንስ ስርአትና የፕሮግራሞች አፈጻጸምን የተመለከቱ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እየመሩ ሲሆን÷ የክልል ጤና ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በውይይቱ እየተሳተፉ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.