Fana: At a Speed of Life!

ለባህል፣ እሴትና አስተዳደራዊ ስርአቶች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር ለመውጣት ለባህል፣ እሴቶች እና አስተዳደራዊ ስርአቶች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ተናገሩ።
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር “ባህላዊ እሴቶቻችን ለሀገራዊ መግባባት” በሚል ሃሳብ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ በሚኒስቴሩ የባህልና ቋንቋ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ባደረጉት ንግግር÷ በባህላችን ውስጥ አብሮነት፣ መደጋገፍ፣ የግጭት መፍቻ መፍትሔዎች መኖራቸውን ጠቁመው÷ እነዚህ እሴቶች በአብሮነት የሚያቆሙን ስለሆኑ ልንጠቀምባቸው እና ልንጠብቃቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ ባህሎች፣ እሴቶች እና ስርአቶች ያላት ሲሆን÷ ከጥንት ጀምሮ በዚህ ባህልና እሴቶች ግጭቶች ሲፈቱ እና ስርአት ሲበጅ መቆየቱ በመድረኩ በቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ ተመላክቷል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ፥ ባህልና እሴቶቻችንን ከትምህርት ጋር በማቆራኘት በማስተማር የሀገራችንን ሰላም ማስፈን እና ችግርን መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡
ባህላዊ ክብረ በዓላት ለሰላም እና ለሕዝብ አብሮነት ያላቸው ፋይዳ እና የጋሞ ባህላዊ እሴቶች ለሰላምና ለሀገራዊ መግባባት ያላቸው ጥቅም በተመለከተ በመድረኩ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በቅድስት ተስፋዬ
ምስል፡- ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.