Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ የጀመረውን የቴክኖሎጂ ማስፋፋት እና የለውጥ ሂደት ከዳር ለማድረስ አብረን እንሰራለን- ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ቴክኖሎጂ ማስፋፋት እና የለውጥ ሂደቱን ከዳር ለማድረስ አብረው እንደሚሰሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸኃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ገለጹ፡፡
በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባልስልጣን ዋና ጸኃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው የኢጋድ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ጎብኝቷል፡፡
ልዑካን ቡድኑ የተቋሙን የሪፎርም ስራዎች በተለይም የመዲናዋን የሰላምና ደህንነት ለመቆጣጠር የሚያገለግለውን የሲሲቲቪ ካሜራ እና በቅርቡ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የተቀየረው ዲጂታል የፖሊስ መገናኛ ራዲዮ፣ እንዲሁም ወንጀልን በቀላሉ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ካሜራ የተገጠመባቸው ዘመናዊ የፓትሮል ተሽከካሪዎችን ተመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል÷ የሲሲቲቪ ካሜራ እና ዲጂታል የፖሊስ ራድዮ መገናኛ እንዲሁም ካሜራ የተገጠመባቸው ዘመናዊ የፖሊስ የፓትሮ ተሽከትካሪዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ዘመናዊ መሆናቸውን ለልዑካን ቡድኑ ገልጸዋል፡፡
ከአፍሪካ አገራት ቴክኖሎጂዎችን በጥቅም ላይ ካዋሉ ጥቂት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗምን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.