Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ያጋጠመውን የአፈር ማዳበሪያ የአቅርቦት ችግርና መፍትሔዎቹ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የ2014/15 የምርት ዘመን ያጋጠመውን የአፈር ማዳበሪያ የአቅርቦት እጥረት እና መፍትሄ ለማስቀመጥ ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው በሀገር አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ እጥረት ማጋጠሙን ገልጸው÷ በምርት ዘመኑ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን ድረስ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ብቻ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የመጣውንም ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በአሁኑ ሰዓት ከማጓጓዝ እና ፍትሀዊ ከሆነ ክፍፍል ጋር በተያያዘ ችግር እየገጠመ በመሆኑ አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ማዘጋጀት ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪ ለአርሷደሩ የብድር አገልግሎቶችን ማመቻቸት የባለድርሻ አካላት ተግባርም ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የውል እርሻ ስምምነት ላይም የክልሉ አርሷደሮች እንዲሠሩ በማድረግ ኢንቨስተሩ ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ግብዓቶች የሚያሟሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ነው ብለዋል።
እነዚህና መሠል የዘርፉ አማራጮችን መውሰድ እንዲያስችል የክልሉ ግብርና ቢሮ ከዞንና ወረዳወች ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በኤልያስ አንሙት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.