ብሪታኒያ ከሩሲያ በሚገቡ የብረት ምርቶች ላይ እገዳ ጣለች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታኒያ ከሩሲያ በሚገቡ አንዳንድ የብረት ምርቶች ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
የለንደን የብረታ ብረት አቅራቢ ድርጅት (ኤልኤምኢ) እንዳስታወቀው ከሩሲያ የሚገቡ ብረቶች በብሪታኒያ መጋዘኖች ውስጥ እንዳይቀመጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡
ብሪታኒያ ካገደቻቸው የብረት ምርቶች መካከልም መዳብ፣ ሊድ፣ የመጀመሪያ ደረጃ አልሙኒየም እና የአልሙኒየም ቅይጥን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
የእገዳ ውሳኔው ከፈረንጆቹ መጋቢት 25 ቀን 2022 በፊት የገቡ የብረት ምርቶችን አያጠቃልልም መባሉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
የብሪታኒያ መንግስት በመጋቢት ወር አጋማሽ ከሩሲያ በሚገቡ የብረት ምርቶች ላይ 35 በመቶ ተጨማሪ ቀረጥ እንደጣለ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!