Fana: At a Speed of Life!

ሶማሊያ የ330 ሚሊየን ዶላር እዳ ስረዛ ተደረገላት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ለሶማሊያ የ330 ሚሊየን ዶላር እዳ ስረዛ መደረጉን አስታወቀ።

እንደ ተቋሙ ገለጻ 100 አበዳሪዎች ለምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የዕዳ ስረዛውን ለማድረግ ተስማምተዋል።

የዕዳ ስረዛው ሶማሊያ በኢኮኖሚ ፕሮግራሟ ባሳየችው መሻሻል የተደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው።

የአሁኑ እርምጃም ሶማሊያ አዳዲስ የገቢ ምንጮች እንድታገኝ ያስችላልም ነው ያለው ተቋሙ ባወጣው መግለጫ።

ሶማሊያ አሁን ላይ 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር እዳ ያለባት ሲሆን፥ ተጨማሪ እዳ ስረዛ ሊደረግላት እንደሚችልም ተቋሙ ፍንጭ ሰጥቷል።

የሶማሊያ አብዛኛው ዕዳ ከፈረንጆቹ 1990 በፊት ሃገሪቱ ለኢንቨስትመንት የተበደረችው መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.