ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ ዕዳቸውን በሩብል የሚከፍሉ “ጠላት” ያለቻቸውን ሀገራት ዝርዝር ይፋ አደረገች

By Alemayehu Geremew

April 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እዳቸውን በሩብል የሚከፍሉና “ጠላት” ብላ የፈረጀቻቸውን ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጋለች፡፡

በሩሲያ በጠላትነት የተፈረጁት ሀገራት ሃያ ሰባቱን የአውሮፓ አባል ሀገራት ጨምሮ ሞናኮ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ እና ሳን ማሪኖ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኒውዝላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ታይዋን እና ማይክሮኔዢያ ናቸው፡፡

ከምዕራቡ የባልካን ሀገራት ደግሞ አልባኒያ፣ ሞንቴኔግሮ እና ሰሜን ሜቄዶኒያ በ”ጠላትነት” ተፈርጀዋል፡፡

በሩሲያ ላይ የሚጣለውን ማዕቀብ የተቃወሙት ሰርቢያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዕጩ አባል ሀገራት አጋርነታቸውን በማሳየታቸው በ”ጠላትነት” አልተፈረጁም ነው የተባለው፡፡

ከላይ በጠላትነት የተፈረጁት ሀገራት ያለባቸውን ማንኛውም ዕዳ በተመቻቸው የባንክ ሥርዓት በሀገሪቷ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል እንዲመልሱ የሩሲያ መንግስት ጠይቋል፡፡

ከዚህ በኋላም ከማንኛውም ድርጅት ጋር የሚደረጉ ስምምነቶች ከሩሲያ መንግሥት ፈቃድ ማግኘት አለባቸው መባሉን የዘገበው ኢውራክቲቭ ነው።

ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ የሩብል ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ እንደነበር ይታወሳል፡፡