የሀገር ውስጥ ዜና

በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ያለውን የስራ ፈላጊዎች መሰረታዊ ጥያቄ ለመፍታት የሚያግዝ ስምምነት ተፈረመ

By Meseret Awoke

April 04, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተሞች በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ያለውን የስራ ፈላጊዎች መሰረታዊ ጥያቄ በጋራ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት የመግባቢያ ስምምነት ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለመግንባት በአጋርነት መስራት በማስፈለጉ መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል።

ከተሞች ያላቸውን ውስብስብ ባህሪ ታሳቢ በማድረግ የቀልጣፋ ምርትና አገልግሎት መፍለቂያ እንዲሆኑ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሻሻል፣ በከፍተኛ መጠን የስራ እድሎችንም ለመፍጠር የሚያግዝ የጋራ ስራ ይጠበቃል ተብሏል።

በስራ ቦታ የሙያ ደህንነትና ጤንነትን የሚያረጋግጡ አገልግሎቶችን ለማስፋፋትም አብሮ መስራቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል ።

\በተመሳሳይ የማዕድን ሚኒስቴር ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በሰው ሀይል ልማት፣ቴክኖሎጂ፣ስራ ፈጠራና የስራ አካባቢ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በበርናባስ ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!