Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው ሸኔ የጦር መሳሪያ ሊያቀብሉ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሲና ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በማዘዋወር ለአሸባሪው ሸኔ ሊያቀብሉ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ወንድወሰን ጀማነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከብሄራዊ መረጃ ደህንነት ጋር በመተባበር መነሻውን ሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ ብሬል ከነሽንሽሉ ትናንት ከቀኑ 9 ሰዓት ደብረ ሲና ከተማ ላይ ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያውን ለአሸባሪው ሸኔ ለማድረስ አቅደው ሲያጓጉዙ እንደነበርም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

የድርጊቱ ፈጻሚዎች የመኪናው ባለቤትና አሽከርካሪው መሆናቸውን የተናገሩት ዋና ኢንስፔክተሩ÷ሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎችንም ይዘው ይጓዙ እደነበር ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይም ግለሰቦቹን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ህብረተሰቡ መሰል አገርና ህዝብ ከሚጎዱ ድርጊቶች በመቆጠብ አጥፊዎችን ሲመለከትም ጥቆማ በመስጠት ከፖሊስ ጋር በትብብር መስራቱን እዲቀጥልም ዋና ኢንስፔክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይም በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 25 በርሜል ቤንዚን በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

25 በርሜል ነዳጁ የተያዘው በአንኮበር ወረዳ ጎረቤላ ከተማ 01 ቀበሌ ትናንት ሌሊት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 30690 አ.አ. አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ተጭኖ ሲጓጓዝ መሆኑንም ተገልጿል።

አሽከርካሪውን ጨምሮ በጉዳዩ የተጠረጡት ሶስት ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ነው የተጠቆመው።

በአበበ የሸዋልዑል

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.