Fana: At a Speed of Life!

ተቋሙ የጤና መድህን አገልግሎቱ ለ43 ሚሊየን ዜጎች ተደራሽ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገር አቀፍ ደረጃ ለ43 ሚሊየን ዜጎች የጤና መድህን አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት አስታወቀ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አዋጅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።
 
በዚህም በረቂቅ አዋጁ ላይ መካተት ያለባቸውን ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ÷በአገር አቀፉ ደረጃ የማህበረሰብ ጤና መድህን ተግባራዊ ከሆነ አንስቶ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል 78 በመቶ በሚሆኑት ላይ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው÷ በዚህም 43 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማና በደቡብ ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም እንዳለ ጠቁመው÷ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያለውን አነስተኛ አፈፃጸም ለማሻሻልም ቀጣይነት ያለው ስራ ይከናወናል ብለዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አብዱላሂ በበኩላቸው÷ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አዋጅ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
መንግስት የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል እና የህክምና መሳሪያ ግብዓት አቅርቦትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል ።
መንግስት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አማካኝነት እንደ ካንሰር፣ የልብና የኩላሊት ያሉ ህክምናዎችን ለህብረተሰቡ በቅርበት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት፡፡
 
ባለፈው በጥር ወር በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 ሚሊየን ዜጎችን የጤና መድን ተጠቃሚ ማድረግ መቻ ሉን የጤና መድን አገልግሎት መግለጹ ይተወሳል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.