Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የትራፊክ አደጋው በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 ላይ የደረሰ ሲሆን÷ ኮድ 3 A02166 አዲስ አበባ የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ፍሬን ተበጥሶ ባደረሰው ጉዳት ህጻናት ተማሪዎችን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ እንደገለጹት÷ ከቁስቋም -ሺሮ ሜዳ በመጓዝ ላይ የነበረ ታክሲ በደረሰበት የፍሬን መበጠስ አደጋ ነው 2 ተማሪዎችን ጨምሮ በ6 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ እንዲሁም 2 ከባድና 2 ቀላል አደጋዎች የደረሰው፡፡
በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠንና መንስኤውን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.