ኢትዮጵያን በተደራጀ መልኩ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን በኬንያ የጋምቤላ ማህበረሰብ ተወላጆች ገለጹ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በተደራጀ መልኩ ለመደገፍ እና ከኤምባሲው ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን በኬንያ የጋምቤላ ማህበረሰብ ተወላጆች ማህበር አባላት ገለጹ፡፡
በናይሮቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ በኬንያ የጋምቤላ ማህበረሰብ ተወላጆች ማህበር ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን÷ የማህበሩን ሊቀ-መንበር ጨምሮ 18 አባላት በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡
ኤምባሲው ተወካዮችን ለማነጋገር ባደረገላቸው ጥሪ መደሰታቸውን የገለጹት የማህበሩ ተወካዮች÷ ኢትዮጵያን በተደራጀ መልኩ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በኤምባሲው የኢኮኖሚ፣ የዳያስፖራ እና የቆንስላ ጉዳዮች አስተባባሪ አምባሳደር ዶክተር ደስታ ወልደዮሐንስ ከማህበሩ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል።
በኤምባሲው የዳያስፖራ ጉዳዮች ዲኘሎማት ወይዘሮ ሰላም አዳም በበኩላቸው÷ ለማህበሩ የኤምባሲው አስፈላጊ ድጋፍ እንደማይለየው ተናግረዋል።
ማህበሩ በኬንያ የኢትዮጵያውያን ጥላ ማህበር ጋር በጋራ መስራቱ ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው በመግለጽ÷ ጊዜ ሳይወስዱ ወደ ማህበሩ እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።
የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ኦጁኒ ኦቻላ እና ሌሎች አባላት ከኤምባሲው ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!