Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ መንግሥት የኢንቨስትመንት መስኩን ለማሳደግ ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ይሰራል – ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በተመለከተ ከባለሀብቶችና ከአጋር ባለድርሻ አካላት ጋር በባሕር ዳር ውይይት እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ክልሉ በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬትና የማዕድንና ሌሎች ሀብቶች ባለቤት መኾኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ለባለሀብቱ የሚሰጠው አገልግሎት ባለሀብቱን የሚያረካ ባለመኾኑ ችግሩን ለመፍታት በትኩረት መሠራት እንዳለበት መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በርካታ ባለሀብቶች የልማት ቦታ ቢሰጣቸውም የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት አለመቻላቸውንም ተናግረዋል።

የኢንቨስትመንት ችግሮች በፍጥነት እንዲሻሻሉ፣ የሥራ እድል በመፍጠር፣ ባለሀብቶችም ለሕዝብ ቃል የገቡትን በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንድሪስ አብዱ ባለፉት ዓመታት የክልሉ መንግሥት ለኢንቨስትመንት ንቅናቄው ትኩረት ሰጥቶ ሲሠራ እንደቆየ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.