Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት የጦር ወንጀል መርማሪዎችን ወደ ዩክሬን ሊልክ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በዩክሬኗ ቡቻ ከተማ የተፈፀመውን የጦር ወንጀል የሚመረምር ቡድን ወደ ዩክሬን ሊልክ መሆኑን አስታወቀ።
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም በቡቻ ተፈፅሟል የተባለውን የጦር ወንጀል የሚያጣሩ መርማሪዎች ወደ ስፍራው እንደሚላኩ ገልጸዋል።
የምርመራ ቡድኑ እንደ ገለልተኛ አካል ሳይሆን ዩክሬን በጉዳዩ ላይ የምታደርገውን ምርመራ የሚያግዝ ነው መባሉን አር ቲ ዘግቧል።
ዩክሬን የሩሲያ ወታደሮች በቡቻ ከተማ ንጹሃንን ገድለዋል በሚል ውንጀላ አቅርባለች።
በአንጻሩ ሩሲያ ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ትንኮሳ ነው በሚል ውንጀላውን ውድቅ አድርጋለች።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.