Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት የንቅናቄ መድረክ ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት የንቅናቄ መድረክ ተከናውኗል፡፡
የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፋለ እንደገለጹት÷ በእንስሳት ዘርፍ እንደ ሃገር ያለው የእንስሳት ሃብት ሰፊ ነው።
ያለውን ሃብት በመጠቀም የሰው ሃብት ላይ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው÷ የተደራጀ የሰው ሃብት አደረጃጀት ማሻሻል ተገቢ መሆኑንም አንስተዋል።
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በበኩላቸው÷ ዘርፉ በብዙ ፈተናዎች የተከበበ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይ ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ ገልጸው÷ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ግብርናው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግብርናው የጀርባ አጥንት ደግሞ የእንስሳት ሃብት ልማት መሆኑን ተናግረዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው በግብርናው ዘርፍ የእንስሳት ዘርፍ አስፈላጊነት ሰፊ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉን ማዘመን እና ሜካናይዝድ ግብርናን ማስፋፋት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
የግብርና ሴክተሩ በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት በማስተናገዱ ዘርፉን እንደገና ለማንሰራራት ለዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ለባለሙያዎች እና ለሚመለከተው ሁሉ ተጨማሪ ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል።
በለይኩን አለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.