Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በተካሄዱ የሕዝብ መድረኮች ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ ይገባል-የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በተካሄዱ የሕዝብ ውይይት መድረኮች ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ገለጹ፡፡
በፓርቲው ድህረ-ጉባዔ በየደረጃው በተካሄዱ የሕዝብ ውይይቶች የተነሱ ጥያቄዎችን መነሻ አድርጎ በተዘጋጀው የ100 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ከክልሉ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ህዝቡ በየደረጃው ያነሳቸው የኑሮ ውድነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ሌብነትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች፣ የልማት እና ሌሎች ጥያቄዎች የዕቅዱ መነሻ ተደርገው መወሰዳቸውን አቶ አብዱጀባር ገልጸዋል፡፡
በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ሕጋዊ እርምጃን በማጠናከር ሰው ሠራሽ የገበያ አቅርቦት ችግርና የኑሮ ውድነትን ማስተካከል የሚያስችሉ ስራዎችን መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በማጠናቀቅ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት የፓርቲው ጽህፈት ቤት ሀሃፊ÷ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ከሌብነትና ከግል ተጠቃሚነት ነጻ በማድረግ የተገልጋዮችን አርካታ ማሳደግ ይገባልም ብለዋል፡፡
በዕቅዱ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ ክትትል እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን÷ ተቋማት ከተሰጣቸው ኃላፊነት ጋር በማጣጣም እቅድ አዘጋጅተው ወደሥራ እንዲገቡም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡
አመራሩ ህዝቡ ያነሰቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ አቶ አብዱጀባር መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ውይይት እንደሚካሔድ የገለጹት ደግሞ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር ናቸው፡፡
በየደረጃው ያለው አመራር ጥያቄዎቹ በጥራት፣ በፍጥነት እንዲመለሱ በቁርጠኝነት እንዲያስፈጽምም አሳስበዋል፡፡
እቅዱ በፓርቲና በመንግስት ጥረት ብቻ ሊፈጸሙ እንደማይችል የገለጹት መክትል ኃላፊው÷ የክልሉ ህዝብ ለእቅዱ ተፈጻሚነት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.