Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ – ሱዳን የወዳጅነት ማህበር “ከዒድ እስከ ዒድ” ጥሪን እንደሚደግፉ ገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ – ሱዳን የወዳጅነት ማህበር የሱዳን ወገን ከዒድ እስከ ዒድ ወደ አገር ቤት ጥሪን እንደሚደግፍ እና ሱዳናውያን ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡
ከኢትዮ-ሱዳን የወዳጅነት ማህበር የሱዳን ወገን ጋር “ከዒድ እስከ ዒድ” ወደ አገር ቤት ጥሪን በተመለከተ በተካሄደ ውይይት÷ ስለጥሪው እና የተዘጋጁ መርሃ ግብሮች ገለፃ ተደርጓል፡፡
በሱዳን የኢፌዴሪ ኤምባሲ የዳያስፖራ ክፍል ኃላፊ አቶ ሚካኤል ጦቢያስ “ከዒድ እስከ ዒድ” ወደ አገር ቤት ጥሪው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያ ወዳጆች የተላለፈ ጥሪ መሆኑን አስታውሰው÷የተለያዩ መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡
በዚህም ሱዳናውያን ተሳታፊ እንዲሆኑ በወዳጅነት ማህበሩ በኩልም ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የወዳጅነት ማህበሩ የሱዳን ወገን በበኩሉ÷ ጥሪውን እንደሚደግፍ በመግለፅ ሱዳናውያንም የጥሪው ተሳታፊ እንዲሆኑ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
በውይይቱ በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለሚደርሰው ችግር ተወያይተው በቀጣይ ችግሮቹን ለመፍታት በጋራ እንደሚሰሩ መገለጹን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.