Fana: At a Speed of Life!

አዳዲስ የቻይና ማዕድን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንዲሳተፉ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ዣው ዢዋን ጋር በማዕድን ዘርፍ አብሮ በመስራት ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ዑማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ከቻይና አምባሳደር ዣው ዢዋን ጋር በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የቻይና ኩባንያዎች ተሳትፎን ለማጠንከርና አዳዲስ የቻይና ማዕድን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ በጋራ ለመስራት ከአምባሳደሩ ጋር መግባባታቸውንም ነው ሚኒስትሩ ያነሱት።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.