Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል በ174 ሚልየን ብር 486 የእርሻ መሳሪያዎችን ሊገዛ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ486 የእርሻ መሳሪያዎችን ለመግዛት ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር ውል ተፈራረመ።
የክልሉ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ነው ከኩባንያው ጋር 162 ትራክተሮች፣ 162 ማረሻ ፣ 162 መከስከሻ ፣ አጠቃላይ የ486 የእርሻ መሳሪያዎች ግዢ ውል የፈፀመው፡፡
በፊርማው ስነ ስርዓቱ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፥ ክልሉ ባለፈው ስርዓት በነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር በግብርናው ላይ ውጤት ያለው ስራ አለመሰራቱን ጠቁመው፥ በቀጣዩ ዓመት የክልሉ መንግስት በግብርናው ዘርፍ ለመስኖ ልማት ትልቅ ትኩረት በመስጠቱ ይህን የዛሬውን የግብርና መሳሪያዎች ግዢ ውል ፈጽሟል ብለዋል ።
በዚህም ክልሉ የውሐና የመሬት እጥረት የሌለበት በመሆኑ ምርትና ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ ውል የተፈረመላቸው የእርሻ መሳርያዎች እንደሚያግዙ መግለፃቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብሁሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው፥ የተደረገው ውል ለክልሉ ግብርና ምርት ላይ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ በመግለጽ ኢትዮ ኢንጂነሪንግም አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል ።
ኩባንያው ከክልሉ መንግስት ቦታ ካገኘ የትራክተር ጥገናና መለዋወጫ ማዕከል መክፈት እንደሚፈልግ፥ ይህም አርሶአደሩ ለጥገናና ለመለዋወጫ የሚያጠፋውን ጊዜና ወጪ እንደሚያስቀር ነው የተናገሩት።
ይህ የዛሬው የ486 የእርሻ መሳሪያዎች ግዢ ውል አጠቃላይ የምርት እሴት ታክስን ጨምሮ 174 ነጥብ 1 ሚልየን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተመላክቷል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.